Fana: At a Speed of Life!

ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) በቱርክ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከተመራ ከፍተኛ ልዑክ ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በቱርክ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቡርሃንቲን ዱራን ከተመራ ከፍተኛ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱም የአንካራ ስምምነት አተገባበርን አስመልክቶ በመጪው ቴክኒካል ድርድር ላይ ምክክር ማድረጋቸውም ነው የተገለጸው፡፡

ጌዲዮን (ዶ/ር) በዚህ ወቅት ፥ ቱርክ በአንካራው ስምምነት ስላደረገችው አስተዋጽዖ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

አክለውም ኢትዮጵያም ስምምነቱን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኗን መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.