Fana: At a Speed of Life!

በኖርዌይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለጠ/ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ ያላቸውን ድጋፍ ለመግለጽ ለኖቤል የሰላም ሽልማት ኮሚቴ ደብዳቤ አስገቡ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኖርዌይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ያላቸውን ድጋፍ ለመግለጽ ለኖቤል የሰላም ሽልማት ኮሚቴ ደብዳቤ አስገቡ።

መቀመጫቸውን ኖርዌይ ያደረጉት እና በተለያዩ ተቋማት ውስጥ በማገልገል ላይ የሚገኙት ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ አሁናዊውን የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ሁኔታ አስመልክተው ነው ደብዳቤውን ያስገቡት።

በደብዳቤያቸውም የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ድግያ ተከትሎ የተፈጸመውን ድርጊት በማውገዝ የመንግስትን የሰላም ጥረት ለማደናቀፍ የተደረገ ሴራ መሆኑን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የሃገሪቱን እድገት እና ብልጽግና ለማረጋገጥ ሌት ተቀን እየሰሩ ይገኛሉ በማለትም ለኮሚቴው በደብዳቤያቸው አስታውቀዋል።

በዚህም ኮሚቴው የኢትዮጵያ መንግስት እያደረገ ያለውን ጥረት እንዲገነዘብ አሳስበዋል።

በተጨማሪም ኮሚቴው ለጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ያበረከተው የሰላም ሽልማት የሚገባቸው መሆኑን ምሁራኑ ጠቅሰዋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.