Fana: At a Speed of Life!

የኮሪደር ልማት ስራን በምሽት ጭምር በማከናወን ተጨባጭ ለውጦች እየተመዘገቡ ነው – አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኮሪደር ልማት ስራዎችን በምሽት ጭምር በማከናወን ተጨባጭ ለውጦች እየተመዘገቡ መሆኑን የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በሐረር ከተማ የኮሪደር ልማት የምሽት ስራ እንቅስቃሴዎችን ተመልክተዋል።

የኮሪደር ልማት፣ የመንገድ ዳር መብራቶች፣ የአባዲር ፕላዛ፣ እና የአረንጓዴ ልማት ስራዎች ላይ የመስክ ምልከታ ማድረጋቸውም ተገልጿል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በጉብኝቱ ወቅት÷ የኮሪደር ልማት ስራው በተቀናጀ መንገድ በምሽት ጭምር ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል ብለዋል፡፡

የኮሪደር ልማት ስራውን በጥራትና ፍጥነት አጠናቆ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ትኩረት መሰጠቱን ገልጸው÷በተለይ ስራዎችን በምሽት ጭምር በማከናወን የስራ ባህልን በማዳበር ተጨባጭ ለውጥ እያሳየ መሆኑን ገልጸዋል።

የኮሪደር ልማቱ ከተማዋን ለኑሮ ምቹ በማድረግ የከተማዎን ነዋሪዎች ተጠቃሚነት ታሳቢ ባደረገ መልኩ እየተሰራ እንደሚገኝም መገለጹን የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በተለይ የሐረር ከተማን ገፅታ ከመቀየር ባለፈ ለበርካታ ወገኖች የስራ እድል በመፍጠር በኢኮኖሚ ተጠቃሚ እያደረገ እንደሚገኝም ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.