Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች ከኮማንዶና አየር ወለድ እዝ የሰራዊት አመራሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኮማንዶና አየር ወለድ እዝ የሰራዊት አመራሮችን በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

የኮማንዶና አየር ወለድ እዝ ዋና አዛዥ ሌ/ጀ ሹማ አብደታ በዚህ ወቅት÷የዓድዋ ድል መታሰቢያ ምንም አይነት ልዩነት ቢኖር በሀገር ጉዳይ በጋራ በመቆም ፈተናዎችን የማለፍ ተምሳሌት መሆኑን ተናግረዋል::

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው÷የኮማንዶ እና አየር ወለድ እዝ የሰራዊት አመራሮች እና ሰራዊቱ ለሀገር እየከፈሉት ላለው ውድ ዋጋ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የዓድዋ ድል መታሰቢያ ለሀገር ውለታ የዋሉ ጀግኖች ቋሚ መታሰቢያ መሆኑንም ነው ያወሱት፡፡

ከውይይቱ አስቀድሞ ከሻለቃ በላይ ያሉ የሰራዊት አመራሮቹ የዓደዋ ድል መታሰቢያን መጎብኘታቸውን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.