Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ የጤና መድህን አገልግሎት ሥራዎች ላይ ያለውን አፈጻጸም በፍጥነት ማሻሻል ይገባል- ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የጤና መድህን አገልግሎት ሥራዎች ላይ ያለውን ዝቅተኛ አፈጻጸም በፍጥነት ማሻሻል እንደሚገባ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) አሳሰቡ፡፡

 

የ2017 በጀት ዓመት ክልላዊ ማህበረሰብ ዓቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት የንቅናቄ መድረክ “የጤና መድህን አገልግሎት ለጋራ ተጠቃሚነት” በሚል መሪ ሃሳብ  ባለድርሻ አካላት በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።

 

የክልሉ ርዕሰ መስተደድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በመድረኩ ላይ እንደገለጹት÷ በክልሉ የጤና መድህን አገልግሎት ሥራዎች አፈጻጸም ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻሎችን ቢያሳይም ከሚጠበቀው ውጤት አኳያ አፈጻጸሙ አነስተኛ ነው።

 

የጤና መድህን አገልግሎት አባላትን ማፍራት እና ነባር እድሳት ሥራዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሰራት እንደሚገባ ተናግረው ሁሉም የጤና መድህን ተግባራት ሙሉ በሙሉ መፈጸም ይጠበቃልም ነው ያሉት።

 

የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ኢብራሂም ተማም በበኩላቸው÷በክልሉ በ2017 ዓ.ም ነባር የአባላት ዕድሳትና አዲስ አባላት ማፍራት ስራ ተጀምሮ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት በየደረጃው የሚገኙ አካላት መረባረብ እንደሚገባቸው መናገራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.