Fana: At a Speed of Life!

ከ740 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ከ740 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል ተመረቀ።

በቦንጋ ከተማ የተገነባው ማዕከል የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እና የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመኒቴ (ዶ/ር) በተገኙበት ተመርቆ መከፈቱን የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።

ማዕከሉ በዓመት ከ150 ሺህ ኩንታል በላይ ዘር ማዘጋጀት የሚያስችል ዘመናዊ የዘር ማበጠሪያ ማሽን፣ የግብርና ግብዓት ማከማቻ መጋዘኖች፣ የእርሻ መሳሪያዎችና ቴክኖሎጂ ማሳያና ዘመናዊ የዘር ቁጥጥር ላብራቶሪን ያካተተ ነው።

ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል እና ከፊል ኦሮሚያና ጋምቤላ ክልሎች የተሟላ የዘርና ግብርና ግብዓት፣ የአፈር ማዳበሪያና ፀረ ተባይ ኬሚካል፣ የእንሳሳት መድኃኒት፣ የተፈጥሮና ኬሚካል ማዳበሪያና የሜካናይዜሽን አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑም ተገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.