የጌዴኦ ብሔር ዘመን መለወጫ “ዳራሮ” በዓል እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጌዴኦ ብሔር ዘመን መለወጫ “ዳራሮ” በዓል ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ሃላፊዎች በተገኙበት በዲላ ከተማ እየተከበረ ነው፡፡
በዓሉ ”ዳራሮ ለአንድነት፣ ለልማትና ለዕድገት” በሚል መሪ ሃሳብ እየተከበረ እንደሚገኝ የክልሉ ከሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።
በአከባበር ሥነ ሥርዓቱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደን ጨምሮ የፈዴራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም የጌዴኦ የባህል መሪዎች እና እንግዶች ተገኝተዋል።