የአይ ኤም ኤፍ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የዓለም የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
ክሪስታሊና ጂዮርጂቫ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ፣ የብሄራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ እና የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጽም አሰፋ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
ማኔጂንግ ዳይሬክተሯ በቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ከሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ጋር በኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እድገት፣ ቅድሚያ በሚሳጣቸው ፖሊሲዎችና በኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ላይ እንደሚመክሩ ይጠበቃል፡፡