Fana: At a Speed of Life!

የሕዝቡን ሰላም ለማረጋገጥ መከፈል ያለበትን መስዋዕትነት ሁሉ ለመክፈል ዝግጁ ነን – ሌ/ጀ ሹማ አብደታ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኮማንዶ እና አየር ወለድ ዕዝ በተሰማራበት በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች እስካሁን ድረስ አባሉ እና አመራሩ ተቀናጅቶ በሰራው ስራ ከፍተኛ ውጤት መገኘቱን የዕዙ አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ሹማ አብደታ ተናግረዋል።

ሌ/ጀ ሹማ አብደታ ከሬጅመንት አመራር በላይ ከሆኑ የክፍሉ አመራሮች ጋር ባደረጉት ውይይት እንደገለጹት÷ በአማራ ክልል ያለው ፅንፈኛ ሃይል በአሁኑ ሰዓት የውጊያ ቁመና ይዞ ቁሞ የመዋጋት አቅም የለውም።

ሽፍታ ሁኖ ከማህበረሰቡ ጋር በመመሳሰል የዘረፋ አማራጭ አድርጎ የማህበረሰቡን ሃብትና ንብረት መዝረፍ ላይ መሰማራቱንም ተናግረዋል።

“እየታገልኩልህ ነው ገንዘብ ሰብስበህ አምጣ” እያለ ህዝብን የሚያሰቃየውን ዘራፊ ቡድን አጥፍተን ህዝባችን በሰላም ወጥቶ እንዲገባ እና የልማት ስራውን በሰላም እንዲሰራ ለማድረግ መከፈል ያለበትን መስዋዕትነት ሁሉ ለመክፈል ዝግጁ ነን ብለዋል።

ፅንፈኛውን ሃይል ሙሉ በሙሉ ለመደምሰስ የሚደረገው ዘመቻ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ማሳሰባቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.