Fana: At a Speed of Life!

የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ዋና ዳይሬክተር የኢትዮጵያን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራ አደነቁ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ዋና ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ የኢትዮጵያ መንግስትን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራ አድንቀዋል፡፡

ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ ከገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ፣ ከብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ እና ከፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ፥ ኢትዮጵያ እየተገበረችው በሚገኘው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ላይ በትኩረት መምከራቸው ተገልጿል፡፡

ከዚህ ባለፈም በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ስለሚከናወኑ ወሳኝ ርምጃዎች ዙሪያ ሃሳብ መለዋወጣቸው ተመላክቷል፡፡

የአይ ኤም ኤፍ ዋና ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ የኢትዮጵያ መንግስት ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረት አድንቀው፤ በማሻሻያው ያሉ ስኬቶችንና ተጠባቂ ግቦችን አንስተዋል።

ምክክሩ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በሆኑት የፊስካል ፖሊሲን የሚያጠናክሩ ሥራዎች እና የፋይናንስ ዘርፉን ለማዘመን በሚከናወኑ አበይት ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑ ተነስቷል።

በዐምደወርቅ ሽባባው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.