Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የኮሪደር ልማት ስራን በፍጥነት ለማጠናቀቅ ይሰራል – ከንቲባ አዳነች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ስራን በፍጥነት ለማጠናቀቅ እንደሚሰራ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ፡፡

ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስርገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፥ የሥድስት ወራት የስራ ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መጠናቀቁን ገልጸዋል፡፡

በግምገማው ባለፉት ሥድስት ወራት መገንባት የጀመርነውን ጠንካራ የስራ ባህል የአመራር ቁርጠኝነትንና ቅንጅትን በማጠናከር እንዲሁም የገቢ አሰባሰብን በማሳደግ በርካታ ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜና በጀት በጥራት አጠናቅቀን ለህዝባችን ግልጋሎት ክፍት አድርገናል ብለዋል፡፡

የሀገርን ክብር በሚመጥን መልኩ ውብ፣ ጽዱ እና ለመኖር ምቹ ለማድረግ የተጀመረው የኮሪደር ልማት ስራ አዲስ አበባን ዓለም አቀፍ የስበት ማዕከል ከማድረግ በተጨማሪ ለነዋሪዎች ምቹ የመኖሪያ አካባቢና ሰፊ የስራ እድል የፈጠሩ፣ አገልግሎትን የሚያሳልጡ ተግባሮች ተከናውነዋል ነው ያሉት፡፡

በዚህም የተቀሩት በቀሪ ወራት በፍጥነት እንደሚጠናቀቁ አስገንዝበዋል፡፡

በቀጣይም የአፈፃፀም ውስንነትን በማስተካከል፣ ማዘመን የጀመርነውን አገልግሎት አሰጣጥን በማጠናከር ቀልጣፋ እና ፈጣን እንዲሁም በቴክኖሎጂ የተደገፈ ተደራሽ በማድረግ፣ ብልሹ አሰራር እና ጉቦኝነትን በመታገል እንዲሁም የገቢ አሰባሰብ እና ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር የተጀመሩ ስራዎችን በጥራትና በፍጥነት ለማጠናቀቅ በትኩረት እንሰራለን ብለዋል::

ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር በመተባበር ድክመቶችንን ከነመንስዔዎቻቸው ተነቅሰው እንዲታረሙ እየተደረገ ለላቀ ውጤታማነት ትጋታቸውን እንደሚቀጥሉም ጠቅሰዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.