Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል ግንባታ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እየተጠናቀቀ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል ግንባታ ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እየተጠናቀቀ መሆኑን ገለጹ፡፡

ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ ፥ የኢትዮጵያን ፈጣን ለውጥ ሊገታው የሚችል ምድራዊ ሃይል የለም ሲሉ ገልጸዋል፡፡

አምና በዚህ ወቅት የዓድዋ ድል መታሰቢያን፤ ዘንድሮ ደግሞ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ፣ ግዙፍ እና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ “አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል” ግንባታን በማጠናቀቅ ላይ እንገኛለን ብለዋል።

ይህ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የኮንቬንሽን እና የኤግዚቢሽን ማዕከል ትላልቅ አህጉር አቀፍ እና ዓለምአቀፍ ሁነቶችን ለማስተናገድ በሚያስችል ደረጃ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን መገምገሙን ጠቁመዋል፡፡

ቀሪ ውስን ሥራዎችን በፍጥነት እና በጥራት ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝም ነው ያነሱት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.