Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ከብሪታንያ የአፍሪካ ሚኒስትር ጀምስ ደድሪጅ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ከብሪታንያ የአፍሪካ ሚኒስትር ጀምስ ደድሪጅ ጋር ተወያዩ።

በውይይቱ ወቅት የውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ፥ ኢትዮጵያ በመጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ ሳኒቴሽንና ሃይጂን፣ በመስኖ፣ በተፋሰስ ልማት እንዲሁም በኢነርጂ ዘርፎች እያከናወነች ስላለችው የልማት ሥራዎች ገለጻ አርገውላቸዋል፡፡

በተጨማሪም የታላቁ የኢትዮጵያ ግድብን አስመልክቶ የግንባታ ሂደቱ አሁን ያለበትን ደረጃ ገለፃ ማድረጋቸውን የውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒቴር ያወጣው መረጃ ያመለክታል።

የህዳሴው ግድብ ለኢትዮጵያ እድገት ያለውን ሚና እንዲሁም ለታችኞቹ ተፋሰስ ሀገሮች የሚኖረውን ጥቅም በዝርዝር ገለጻ አድርገውላቸዋል።

የብሪታንያ የአፍሪካ ሚኒስትር ጀምስ ደድሪጅ በበኩላቸው፥ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ድርድር የሦስቱንም ሀገሮች ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ እንዲጠናቀቅ ፍላጎታቸው መሆኑን ገልጸዋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.