የአማራ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን ፣ 9ኛ መደበኛ ጉባዔ መካሄድ ጀምሯል፡፡
ከዛሬ ጀምሮ እስከ የካቲት 7 ቀን 2017 ዓ.ም የሚካሄደው የምክር ቤቱ ጉባዔ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ እንደሚመክር ተመላክቷል፡፡
በዚህ መሰረትም የክልሉ የአስፈፃሚ አካላት የ2017 ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ በስፋት በመምከር ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
እንዲሁም የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የግማሽ ዓመት ሪፖርት፣ የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ኦዲት ላይ በመምከር ቀጣይ አቅጣጫ እንደሚያስቀመጥ መጠቆሙን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የንጋት ኮርፖሬት የ2024 ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለምክር ቤቱ ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ተገልጿል።
በተጨማሪም በሚቀርቡ የተለያዩ አዋጆች ላይ ምክር ቤቱ በስፋት በመምከርና ልዩ ልዩ ሹመቶችን በማጽደቅ እንደሚጠናቀቅ ተጠቅሷል፡፡