ኢትዮጵያ ለ644 ደቡብ ሱዳናዊያን ነጻ የትምህርት ዕድል ሰጠች
አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በ2024/25 የትምህርት ዘመን ለ644 ደቡብ ሱዳናዊያን ነጻ የትምህርት ዕድል ሰጠች፡፡
ነጻ የትምህርት ዕድሉ ለ577 የመጀመሪያ ዲግሪና ለ67 ድሕረ-ምረቃ ፕሮግራም መሰጠቱን በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል መሐዲ ተናግረዋል፡፡
አምባሳደሩ የነጻ ትምህርት ዕድሉ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነትና አጋርነት የሚያጠናክር መሆኑን አንስተው÷ተማሪዎቹ የኢትዮጵያና የደቡብ ሱዳንን ግንኙነት እንዲያጠናክሩ አሳስበዋል፡፡
በደቡብ ሱዳን በከፍተኛ ትምህርት፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የትምህርትና ስልጠና ዳይሬክተር ጀኔራል ፕሮፌሰር ቶች ሌይም በበኩላቸው ÷ ኢትዮጵያ በትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ለደቡብ ሱዳን ለሰጠችው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡
የተማሪዎች ተወካዮችም ለተደረገላቸው የነጻ ትምህርት እድል ተጠቃሚነት ምስጋና አቅርበው÷ለሁለቱ እህትማማች ሀገራት የጋር ተጠቃሚነት እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል፡፡