አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከአልጄሪያ አቻቸው ጋር መከሩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከአልጄሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ ሰልማ ባህታ መንሱሪ ጋር በሁለቱ ሀገራት የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
ሚኒስትር ዴኤታዎቹ በአካባቢያዊ እና አህጉራዊ ሰላም እና ጸጥታን አስመልክተው መወያየታቸው ተገልጿል፡፡
አምባሳደር ምስጋኑ ከአልጄሪያ አቻቸው ጋር የሁለቱን አገራት የሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ግንኙነቶች የበለጠ ማጠናከር በሚቻልባቸው መስኮች ላይም መምከራቸውን ከሚኒስቴሩ ገኘነው መረጃ ያመላክታል።