ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ የመንገድ መሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በሰሜናዊ እና በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን የመንገድ መሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች የግንባታ ሂደትን ጎብኝተዋል፡፡
የመንገድ መሰረተ ልማት ፕሮጀክቶቹ በክልሉ እና በፌዴራል መንግስት ወጪ የሚገነቡ መሆናቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።
በጉብኝቱ ላይ ርዕሰ መስተዳድሩን ጨምሮ የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አብርሃም ማርሻሎ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።