የኢትዮ-ጅቡቲ ኮሪደር አስተዳደር ባለስልጣን የምስረታ መድረክ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮ-ጅቡቲ ኮሪደር አስተዳደር ባለስልጣን የምስረታ መድረክ በቢሾፍቱ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) እንደተናገሩት÷ ኮሪደር አስተዳደር ባለስልጣን መመስረቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የመሰረተ-ልማት ዝርጋታን በዘመናዊ መንገድ የቁጥጥር ስርዓት በመታገዝ የተሻለ የንግድ ልውውጥ ለማድረግ ያስችላል።
የሁለቱን ሀገራት የንግድ ግንኙነት ይበልጥ በማጠናከር እና በዘርፉ የሚስተዋለውን ህገ-ወጥ ንግዶችን በመቆጣጠር ህጋዊ የንግድ ስርዓት እንዲስፋፋ በማድረግ ረገድ የጎላ አስተዋፅዖ እንዳለው አንስተዋል።
የሁለቱን ሀገራት የትራንስፖርት ተቋማት በማቀናጀት ወደ ተሻለ የንግድ ምዕራፍ እንደሚወስድ መናገራቸውንም በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።
የጅቡቲ መሰረተ-ልማት እና ኢኪዩፕመንት ሚኒስትር ሀሰን ሀሙድ÷ የጅቡቲ ንግድ እና ቱሪዝም ሚኒስትር መሀመድ ዋርሳማ እና ሌሎች የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በመድረኩ ተገኝተዋል።