Fana: At a Speed of Life!

የሕብረቱ ተቋማዊ ሪፎርም መሰረታዊ ለውጥ በሚያመጣ መልኩ እየተከናወነ ነው – ሙሳ ፋኪ ማህማት

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2017(ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ ሕብረት ተቋማዊ ሪፎርም መሰረታዊ ለውጥ በሚያመጣ መልኩ እየተከናወነ መሆኑን የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሙሳ ፋኪ ማህማት ገለጹ።

46ኛው የአፍሪካ ሕብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብስባ እየተካሄደ ነው።

ሊቀ መንበሩ በስብሰባው÷የአፍሪካ ሕብረት በሊቀመንበርነት ዘመናቸው በኢኮኖሚ በተለይም በግብርናው ዘርፍእና በማህበራዊ መስኮች የአፍሪካን አንድነት የሚያጠናክሩ ተግባራት ማከናወናቸውን ጠቅሰዋል።

የአህጉራዊ ተቋማዊ ሪፎርምን ጨመሮ በሃላፊነት ዘመናቸው የተከናወኑ የሪፎርም ስራዎች ተጨባጭ ለውጥ ማስመዝገባቸውን ገልጸዋል።

የአፍሪካ ሕብረት ተቋማዊ ሪፎርም መሰረታዊ ለውጥ በሚያመጣ መልኩ እየተከናወነ ነውም ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በሌላ በኩል አህጉራዊ ሰላምና ጸጥታ አሁንም ትኩረት የሚሻ ጉዳይ እንደሆነ ነው ሊቀ መንበሩ የተናገሩት፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.