Fana: At a Speed of Life!

የጤና ፖሊሲ ማሻሻያ በማድረግ በሽታን ቀድሞ የመከላከል አቅምን ማሳደግ መቻሉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አካታችነትን ማዕከል ያደረገ የጤና ፖሊሲ ማሻሻያ በማድረግ በሽታን ቀድሞ የመከላከልና አክሞ የማዳን አቅምን ማሳደግ መቻሉን የብልጽግና ፓርቲ ም/ቤት አባልና የጤና ሚኒስትር ዴዔታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ ገለጹ፡፡

ዶ/ር ደረጄ የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ አካታች ማህበራዊ ልማትን ማረጋገጥ፣ የጤና ማህበራዊ ብልጽግናን እውን ለማድረግ በሚል ባስቀመጠው አቅጣጫ ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በማብራሪያቸውም ብልፅግና ፓርቲ ባለፉት 3 ዓመታት ተቋምን ከመገንባትና በማህበረሰቡ ዘንድ የተሻለ ቅቡልነትን ለማግኘት አዳዲስ እሳቤዎች በማብቃት ከፍተኛ አድናቆት የሚሰጣቸውን ትላልቅ ስኬቶችን አስመዝግቧል ብለዋል፡፡

ፓርቲው ሰው ተኮር በመሆን ተከታታይነት ያለው እድገት ማምጣት መቻሉን ጠቁመው÷አረጋውያንን፣ አካል ጉዳተኞችንና አቅመ ደካሞችን በተለያዩ መርሐ ግብሮች ሰፋፊ ማህበራዊ ስራዎች መስራቱን አስታውሰዋል፡፡

አካታችነትን ማዕከል ያደረገ የጤና ፓሊሲ ማሻሻያ በማድረግ በሽታን ቀድሞ መከላከልና አክሞ የማዳን አቅምን ከፍ ማድረግ መቻሉንም ጠቁመዋል፡፡

ፓርቲው ለጤና ሴክተሩ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ኢትዮጵያ የሜዲካል ቱሪዝም ማዕከል እንድትሆን በርካታ ሥራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡

የመድሃኒትና የሕክምና መሳሪያ በሀገር ውስጥ የማምረት አቅምን በማሳደግ ማህበረሰቡ ያለ ምንም ወጪ ወደ ሕክምና ተቋም ሄዶ ሕክምናን በፈለገበት ጊዜ እንዲያገኝ ማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ስርዓትን ወደ ስራ ማስገባት መቻሉን አብራርተዋል፡፡

ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት ሶስት ዓመታት በፓለቲካ፣ በማህበራዊ በኢኮኖሚ እንዲሁም በውጭ ግንኙነት ከፍተኛ ውጤት እንዳስመዘገበ አጽንኦት መስጠታቸውንም የፓርቲው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.