Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና ጸጥታ ምክር ቤት አባል ሆና ተመረጠች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና ጸጥታ ምክር ቤት አባል ሆና መመረጧን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ዛሬ በተጀመረው 46ኛው የአፍሪካ ሕብረት መደበኛ የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ በተካሄደው ምርጫ ነው ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና ጸጥታ ምክር ቤት አባል ሆና የተመረጠችው።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሰላም እና ጸጥታ እንዲሁም እድገት ዙሪያ እያበረከተችው ላለው አስተዋጽኦ እውቅና የሚሰጥ ነውም መባሉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.