Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ ሚ ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከጋቪ ዋና ስራ አስፈጻሚ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከ38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ጋቪ- ቫክሲን አሊያንስ ከተባለ የጤና አጋር ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ ሳኒያ ኒሽታር ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸው ኢትዮጵያ ከድርጅቱ ጋር በበሽታ መከላከል ጥረቶች፣ በጠንካራ ጤና ስርዓት ግንባታ እንዲሁም በኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ የሽግግር ዕቅድ ዙሪያ ትብብራቸውን ለማጠናከር መክረዋል።
ጤናማ ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ በሚደረገው ጥረት የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ይበልጥ እንደሚጎለብት እምነታቸውን ገልጸዋል።
ጋቪ በጤናው ዘርፍ በተለይም በታዳጊ ሀገራት የክትባት አቅርቦት ላይ አበክሮ የሚሰራ ዓለም አቀፍ ድርጅት ነው።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.