መሀሙድ የሱፍ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቀድሞው የጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል፡፡
የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ለመሆን የኬንያው ራይላ ኦዲንጋ፣ የማዳጋስሩ ሪቻርድ ራንዲሪያማንድራቶ እና የጅቡቲው ማህሙድ አሊ ዩሱፍ በእጩነት ቀርበው ነበር፡፡
በዚህ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን በሊቀመንበርነት ሲመሩ የቆዩትን ሙሳ ፋኪ መሀመትን ለመተካት በተካሄደው ምርጫ የጅቡቲው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ አሸንፈዋል።