Fana: At a Speed of Life!

ክሪፕቶ እና ብሎክቸይንን የተመለከተ ሁነት በሳይንስ ሙዚየም ተካሄደ

 

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በፋኖስ ቴክ አዘጋጅነት ክሪፕቶ እና ብሎክቸይንን የተመለከተ ሁነት በዛሬው እለት በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሙዚየም ተካሂዷል።

 

ሁነቱ ብሎክቸይንን በመጠቀም ለኢትዮጵያ ምን መስራት እንችላለን? በሚለው ላይ የበለጠ ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ እንደሆነ ተገልጿል።

 

የፋኖስ ቴክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ቴዎድሮስ ስንታየሁ÷ ድርጅታቸው ስለብሎክቸይን ለወጣቶች እውቀት የማስጨበጥ ስራ እንደሚሰራ እና ከዓለም አቀፍ የብሎክቼይን ድርጅት ከሆነው ባይቢት ጋር እንደሚሰሩ አመልክተዋል።

 

ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለውም ብሎክቼይንን በመጠቀም በርካታ ወጣቶች ጥቅም እያገኙበት እንደሆነም አስረድተዋል።

 

በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት የብሎክቸይን ቴክኖሎጂ የጥናት እና ልማት ላይ የሚሰሩት አቶ ናኦል ብርሀኑ በበኩላቸው÷ የክሪፕቶ ማይኒንግ ስራ ለሀገር የምንዛሬ ገቢ እንደሚያስገኝ ገልፀው የክሪፕቶ ምንዛሬን ለመገበያያነት ማዋልን በተመለከተ ግን ስጋቶች በመኖራቸው ጥናቶች እየተደረጉ እንደሆነ አመላክተዋል።

 

በዮናስ ጌትነት

 

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.