Fana: At a Speed of Life!

ከተለያዩ መሪዎች ጋር በቁልፍ ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደረግንበት ውጤታማ ቀን ነበር – ጠ/ ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ የመጀመሪያ ቀን ከተለያዩ መሪዎች ጋር በቁልፍ ቀጣናዊ፣ አኅጉራዊ እና በቀዳሚ የልማት ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደረግንበት ውጤታማ ቀን ነበር ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትሰስር ገጻቸው ÷ከኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዚዳንት ቴዮዶር ኦቢያንግ ንጉዬ ማምባሶንጎ፣ ከደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ብሎም ከቦትስዋናው ፕሬዚዳንት ዱማ ቦኮ ጋር ትብብሮቻችንን በምናጠናክርባቸው መንገዶች ላይ ቁርጠኝነታችንን አረጋግጠናል ነው ያሉት።

ከሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ እና ከታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉህ ሀሰን ጋርም የአፍሪካን እድገት ለማፋጠን የጋራ ጥረቶችን ለማጠናከር መወያየታቸውን ገልፀዋል፡፡

ከመንግሥታትም ባሻገር ከግሎባል ፈንድ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ፒተር ሳንድስ እና ከጂኤቪአይ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሳኒያ ኒሽታር ጋር የጤናውን ዘርፍ በማጠናከር ሥራ ላይ መወያታቸውን አውስተዋል፡፡

ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት አኪንዊሚ አዲሴና እና አይኤፍኤዲ ፕሬዚዳንት አልቫሮ ላሪዮ ጋርም የኢትዮጵያን የግብርና ዘርፍ የሚያጎለብቱ ጉዳዮችን አንስተን ተነጋግረናል ብለዋል፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ(ዶ/ር)።

ከንግዱ ዘርፍም ከአሊኮ ዳንጎቴ እና ቶኒ ኢሉሜሉ ጋርም የግሉ ዘርፍ የአፍሪካን እድገት በመምራት ረገድ ስላለው ሚና መምከራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በጽሁፋቸው አስፍረዋል፡፡

በነዚህ ውይይቶች ላይ በመመሥረትም የጋራ ብልፅግናን ለማሳካት እንሠራለን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.