Fana: At a Speed of Life!

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለአፍሪካ ቀዳማዊ እመቤቶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሐግብር አከናወኑ

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለ29ኛዉ የአፍሪካ ቀዳማዊ እመቤቶች የልማት ተቋም ጠቅላላ ጉባኤ አዲስ አበባ የሚገኙ የአፍሪካ ቀዳማዊ እመቤቶች ከስብሰባው ጎን ለጎን በብሔራዊ ቤተ-መንግስት የምሳ ግብዣ እና ጉብኝት አካሂደዋል።

ለአፍሪካ ቀዳማዊ እመቤቶች በቤተ-መንግስት አቀባበልና ግብዣ ያደረጉት ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከሀገረኛ የሙዚቃ ዝግጅት ጀምሮ የኢትዮጵያን የሐገረ መንግስት ሂደት፣የደረጀ የዲፕሎማሲ ስራ፣ የስልጣኔና እምቅ ታሪክ የሚታይበትን የብሔራዊ ቤተ-መንግስት አስጎብኝተዋል፡፡

ኢትዮጵያ የአፍሪካ የስልጣኔና መጻኢ ልዕልና መስኮት መሆኗን ከብዙ ማሳያዎች አንዱ የብሔራዊ ቤተ-መንግስት እንዲሁም በውስጡ የያዛቸው ቅርሶችና ቀደምት ሁነቶች መሆኑን ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ቆይታ ያደረጉ የአፍሪካ ቀዳማዊ እመቤቶች ገልጸዋል።

ቀዳማዊ እመቤቶቹ አክለውም ኢትዮጵያ ለአፍሪካውያን መያያዝና አብሮ መቆም የምታደርገው ጥረት ሁሌም የሚደነቅ መሆኑን ጠቅሰው የተደረገላቸው የክብር አቀባበል ሁልጊዜም የማይረሱት መሆኑን ነው ያነሱት።

ዛሬ የጀመረው 29ኛው የአፍሪካ ቀዳማዊ እመቤቶች የልማት ተቋም ጉባኤ ነገ ቀጥሎ ሲካሔድ በአካታችና የአህጉሩን መልማት የሚያረጋግጡ አጀንዳዎች ላይ እንደሚመክር ይጠበቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.