ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ለተሰናባቹ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽነር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ምስጋና አቀረቡ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለተሰናባቹ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽነር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ምስጋና አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷ “አዲሱን የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበርን በክብር ተቀብለናል፤ ተሰናባቹ ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት፣ ባለፉት ዓመታት ላሳዩት አመራር እና ወዳጅነት ምስጋናዬን አቀርባለሁ” ሲሉ አስፍረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመልዕክታቸው÷” ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ያደረጉትን ያላሰለሰ ጥረት የምታደንቅ ሲሆን በወደፊት ጉዞዎም መልካሙን ትመኛለች” ብለዋል።