የሀገር ውስጥ ዜና

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከብሪታንያ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

By Tibebu Kebede

July 29, 2020

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 22 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከብሪታንያ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ጀምስ ደድሪጅ ጋር በሁለትዮሽ የሃገራቱ ግንኙነት መጠናከር እና ሌሎች የጋራ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሶስት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ የሚገኙትን የብሪታንያ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ጀምስ ደድሪጅን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በዚህ ወቅትም በሁለትዮሽ የሃገራቱ ግንኙነት እና በሌሎች የጋራ ጉዳዮች ላይ ምክክር አድርገዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም የኮሮና ቫይረስ ወረሽኝን ለመዋጋት በሚደረግ ትብብርና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ወረርሽኙን ለመከላከል በርካታ ጠንካራ እርምጃዎች መወሰዳቸውን ገልጸዋል።