የሀገር ውስጥ ዜና

ባለፉት 24 ሰዓታት 915 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ11 ሰዎች ህይወት አልፏል

By Feven Bishaw

July 31, 2020

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ለ8 ሺህ 957 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርምራ ተደርጎ 915 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

በዚህም በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 17ሺህ 530 የደረሰ ሲሆን ከእነዚህ መካከል ቫይረሱ ያለባቸው 10 ሺህ 304 ሰዎች የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል ብለዋል።