ዓለምአቀፋዊ ዜና

በሜክሲኮ በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከ46 ሺህ አልፏል

By Tibebu Kebede

August 01, 2020

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 25 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በሜክሲኮ በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከ46 ሺህ አልፏል፡፡

አሁን ላይ በሃገሪቱ 424 ሺህ 637 ሰዎች ቫይረሱ ሲገኝባቸው 46 ሺህ 688 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል ተብሏል፡፡

ይህን ተከትሎም በቫይረሱ ለህልፈት በተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከአሜሪካ እና ብራዚል ቀጥላ ሶስተኛዋ ሃገር ሆናለች፡፡

የሃገሪቱ የተለያዩ ግዛት አስተዳዳሪዎች ደግሞ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር ሪፖርት ከተደረገው በላይ መሆኑን ይናገራሉ፡፡

መንግስት የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር ያደረገው ጥረትም አነስተኛ ነው በሚል በሃገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ላይ ትችት ሰንዝረዋል፡፡

ምንጭ፣ ቢቢሲ