ከተጋን ኢትዮጵያ ከመረዳት አልፋ ሌሎችን መርዳት ትችላለች – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ተግተን መሥራት ከቻልን ኢትዮጵያ ከመረዳት አልፋ ሌሎችን መርዳት ትችላለች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ዛሬ በምሥራቅ ሐረርጌ ቆላማ አካባቢዎች እየለማ የሚገኝ የበጋ ስንዴ ልማትን ተመልክተናል ብለዋል።
መትጋት፣ መሥራት እና ማየት ከቻልን ኢትዮጵያ ከመረዳት አልፋ ሌሎችን መርዳት ትችላለች ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡
ይህን ሥራ አጠናክረን እንድንቀጥል ሲሉም የአደራ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡