Fana: At a Speed of Life!

የጅግጅጋ ከተማ የመጀመሪያው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ሥራ እየተጠናቀቀ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጅግጅጋ ከተማ የመጀመሪያው ምዕራፍ የ10 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ሥራ በአንድ ወር ውስጥ እንደሚጠናቀቅ የሶማሌ ክልል የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ገለጸ።

የቢሮው ሃላፊ አህመድ ሽኩሪ የኮሪደር ልማት ሥራው በአራት አቅጣጫ እና በስድስት ኮንትራክተሮች እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፤ የሚቀረው የማስዋብ ሥራ እንደሆነ ተናግረዋል።

በሶማሌ ክልል ከለውጡ በኋላ በተሰጠው ትኩረት የኮሪደር ልማቱን ጨምሮ በርካታ የልማት ሥራዎች እየተሠሩ መሆናቸውን አዘንስተው፤ ከ60 በላይ የአስፓልት መንገድ በመከናወን ላይ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

አሁን ላይ የኮሪደር ልማት ሥራዎች የጅግጅጋ ከተማ ገጽታ የሚቀይርና ለከተማዋም እድገት ዕድል ይዞ የመጣ መሆኑን አንስተዋል።

ከኮሪደር ልማት ጎን ለጎን በርካታ ግንባታዎች እየተሰሩ መሆኑን ያነሱት አቶ አህመድ ሽኩሪ፤ ከ12 ሺህ በላይ ዜጎች የሥራ እድል እንደተፈጠረላቸውና ባለሀብቶች መዋለ ነዋያቸውን በኢንቨስትመንት ላይ እንዲያውሉ እድል መስጠቱን ጠቁመዋል።

በታሪኩ ለገሰ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.