Fana: At a Speed of Life!

በ298 ሚሊየን ብር ለሚገነባው የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሶማሌ ክልል ሊበን ዞን ጉራዳሞሌ ወረዳ ከ298 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለሚገነባው የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ።

በሥነ-ሥርዓቱ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) እና ሌሎች የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

ባለብዙ መንደር የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ከ32 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግና በ21 ወራት ተገንብቶ እንደሚጠናቀቅ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.