Fana: At a Speed of Life!

አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ ለማግኘት መስራት አለባት – ፕሬዚዳንት ታዬ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ ለማግኘት መስራት አለባት ሲሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ገለጹ።

አዲሱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐመድ አሊ ዩሱፍ ስልጣናቸውን ከቀድሞ የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ተረክበዋል።

በርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ እንደተናገሩት፤ አፍሪካን ያካተተ ዓለም አቀፋዊ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት እውን የሚሆነው አፍሪካ በጸጥታው ምክር ቤት ተገቢውን ቦታ ስታገኝ ነው።

በመሆኑም በሚወሰኑ ውሳኔዎች ላይ የአፍሪካ የዳር ተመልካችነት ማብቃት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

በተለይም በሰላም፣ በጸጥታ እና በልማት አጀንዳዎች ላይ የውሳኔ ሰጪ አካላት ውስጥ አፍሪካ በቀጥታ ተሳታፊ መሆን እንዳለባት ገልጸዋል።

ይህ እውን እንዲሆን አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንድታገኝ የተጀመረው እንቅስቃሴ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስረድተዋል።

የተጀመረው ጥረት እውን እንዲሆን ኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ ለመቀጠል ቁርጠኝነቱ እንዳላት ገልጸው፤ ለአዲሱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አመራር ውጤታማነት ኢትዮጵያ የድርሻዋን እንደምትወጣ አረጋግጠዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.