ኢትዮጵያና ሩዋንዳ በወታደራዊ ዘርፍ በትብብር ለመስራት ተፈራረሙ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያና ሩዋንዳ በተለያዩ ወታደራዊ መስኮች በጋራ መስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና የሩዋንዳ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ሙባረክ ሙጋጋ ተፍራርመዋል።
የመከላከያ ውጭ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክተር ሜ/ጄ ተሾመ ገመቹ ÷ኢትዮጵያና ሩዋንዳ በልዩ ልዩ ወታደራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለረጅም ዓመታት ሲሰሩ መቆየታቸውን አንስተዋል፡፡
አሁን ላይም የነበረውን ሁለንተናዊ ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር መስማማታቸውን ነው የገለጹት፡፡