ኢትዮጵያና ኩባ በተለያዩ ዘርፎች የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እና ኩባ በተለያዩ ዘርፎች በትብብር መሥራት የሚያስችሏቸውን የመግባቢያ ስምምነቶች ተፈራርመዋል፡፡
የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ከኩባ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሩኖ ኤድዋርዶ ሮድሪጌዝ ፓሪላ ጋር የባህል ዘርፍ ትብብርን ለማጠናከር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመዋል።
በተመሳሳይ ሁለቱ ሀገራት በቴክኖሎጂ፣ ኢነርጂና ኢኖቬሽን ዘርፎች በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመዋል።
ስምምቱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) እና በኢትዮጵያ የኩባ አምባሳደር መይሊን ሱዋሬዝ አልቫሬዝ ፈርመውታል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በዚሁ ወቅት፤ ኢትዮጵያና ኩባ የረጅም ጊዜ የሁለትዮሽ ግንኙነት እንዳላቸው ጠቁመዋል።
የኩባ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሩኖ ኤድዋርዶ ሮድሪጌዝ ፓሪላ በበኩላቸው÷ በኢትዮጵያ የተሳካ ቆይታ እንደነበራቸው ገልጸው፤ የሁለቱ ሀገራት የረጅም ዘመናት ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።