የሀገር ውስጥ ዜና

በቦሌ ክፍለ ከተማ በዛሬው ዕለት ብቻ ከ4 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ የቦንድ ግዢ ተፈፀመ

By Tibebu Kebede

August 02, 2020

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 26፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) በቦሌ ክፍለ ከተማ በተካሄደው መርሃ ግብር ከ4 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ የቦንድ ግዢ ተካሄደ።

“ግድቡ የእኔ ነው” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ስነ ስርዓት የክፍለ ከተማውና የወረዳ አስተዳደር አመራሮች፣ አርቲስቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ አርሶ አደሮች እና ሌሎች ነዋሪዎች የቦንድ ግዢ ፈፅመዋል።