የሀገር ውስጥ ዜና

በአዲስ አበባ 102 ህገ-ወጥ ሽጉጦችና ሌሎች የጦር መሳሪያዎች ተያዙ

By Feven Bishaw

August 03, 2020

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 27፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ)በአዲስ አበባ ከተማ 102 ህገ-ወጥ ሽጉጦችና ሌሎች የጦር መሳሪያዎች መያዙን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ጀይላን አብዲ እንደተናገሩት፤ በመዲናዋ በተለምዶ ኮልፌ 18 ማዞሪያ እና ሰሜን ማዘጋጃ’ በሚባሉ አካባቢዎች ተጠርጣሪው ግለሰብ በተከራይዋቸው ቤቶች ውስጥ ነው ህገወጥ መሳሪያዎቹ የተያዙት።