የሀገር ውስጥ ዜና

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ለኢ/ር ታከለ ኡማ የዕውቅና ሽልማት አበረከተ

By Meseret Demissu

August 04, 2020

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 28 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ኢንጂነር ታከለ ኡማ ወደ ኃላፊነት ከመጡበት ጊዜ አንስቶ ላከናወኗቸው ውጤታማ ስራዎች የዕውቅና ሽልማት አበርክቷል።

ምክር ቤቱ ኢንጂነር ታከለየዕውቅና ሽልማቱ ያበረከተላቸው ÷ የሚሰሩ ስራዎች የከተማዋ ነዋሪዎችን ያማከለ እንዲሆን በማድረግ በኩል ውጤታማ ስራዎችን በማከናወናቸው ፣አስታዋሽ አጥተው ለዘመናት የተዘነጉ የማህበረሰብ ክፍሎችን ማዕከል ያደረጉ ስራዎችን በመስራት ላበረከቱት አስተዋጽኦ መሆኑ ተገልጿል።