የሀገር ውስጥ ዜና

የጊቤ 3 የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ግድብ እየሞላ በመምጣቱ ውሃ ከግድቡ በየደረጃው እንደሚለቀቅ ተገለፀ

By Tibebu Kebede

August 05, 2020

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጊቤ 3 የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ግድብ እየሞላ በመምጣቱ ውሃ በየደረጃው ለመልቀቅ የሚያስችል የሙከራ ስራ ተከናውኗል፡፡

ይህም ከግድቡ የሚለቀቀው ዉሃ ወደፊት በታችኛው ተፋስስ ላይ ጎርፍ እንዳያስከትል ለመቆጣጠር እና ውሃውን በተመጠነ መልኩ በመልቀቅ በክረምቱ መጨረሻ ላይ ግድቡ ሙሉ እንዲሆን ለማድረግ መሆኑን የጣቢያው ስራ አስኪያጅ አቶ ሃብታሙ ሰሙ ገልፀዋል፡፡