Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሜሪካ ለኢትዮጵያ ላበረከተችው የመተንፈሻ ቬንትሌተሮች ድጋፍ ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ ፣ሐምሌ 29 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስር ዐቢይ አህመድ አሜሪካ ለኢትዮጵያ ላበረከተችው የመተንፈሻ ቬንትሌተሮች ድጋፍ ምስጋና አቀረቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ኢትዮጵያ የኮቪድ 19ን ወረርሽኝ ለመከላከል የምታደርገውን ጥረት ለማገዝ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን 250 የመተንፈሻ ቬንትሌተሮች እና ሌሎች ወሳኝ የሕክምና መገልገያዎች ድጋፍ ስላደረጉልን፣ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥትን አመሰግናለሁ ብለዋል።

እነዚህ መገልገያዎች የደረሱን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ብዛት በጨመረበት አሳሳቢ ጊዜ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተመጣጣኝ የመከላከል እርምጃዎችን መውሰዳችን እንዳለ ሆኖ፣ መዘናጋት እና ቸልታንም እናስወግድ በማለት አሳስበዋል።

አሜሪካ ኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ 250 ሜካኒካል ቪንቲሌተሮች ድጋፍ ማድረጓ የሚታወስ ነው።

ድጋፉን በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምሳደር ማይክል ራይነር ለጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በትናትናው ዕለት አስረክበዋል።

የሜካኒካል ቬንቲለተር የአንዱ ዋጋ 8 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ሲሆን÷ አጠቃላይ ዋጋ 70 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.