የሀገር ውስጥ ዜና

በበዓል ሰሞን በነበሩ መዘናጋቶችና ጥንቃቄ በጎደላቸው ህዝባዊ ሰልፎች የኮሮና ቫይረስ መስፋፋቱ ተገለጸ

By Meseret Demissu

August 06, 2020

አዲስ አበባ ፣ሐምሌ 30 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የበዓል ሰሞን የነበሩ መዘናጋቶች የፈጠሯቸው ንክኪዎች እንዲሁም ህብረተሰቡ ያለጥንቃቄ ሲሳተፍባቸው የነበሩ ሰልፎች አሁን ላለው የኮሮና ቫይረስ መስፋፋት ምክንያቶች መሆናቸውን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሳሕርላ አብዱላሂ ÷የኮሮና ቫይረስ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ ከታወቀ ጊዜ ጀምሮ የነበሩ ጥንቃቄዎች እና መከላከሎች አሁን ላይ እየተቀዛቀዙ መምጣታቸውን ገልጸዋል ።