ስፓርት

በዩሮፓ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ተፋላሚዎች ተለይተዋል

By Tibebu Kebede

August 07, 2020

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 1 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በዩሮፓ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ተፋላሚዎች ተለይተዋል፡፡

ከትናንት በስቲያ እና ትናንት በተደረጉ የጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታዎች በሩብ ፍጻሜ የሚጫወቱ 8 ቡድኖች ታውቀዋል፡፡

የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎቹ የፊታችን ሰኞ እና ማክሰኞ የሚደረጉ ይሆናል፡፡

ሰኞ ማንቼስተር ዩናይትድ ከዴንማርኩ ኮፐንሃገን እንዲሁም የጣሊያኑ ኢንተርሚላን ከጀርመኑ ባየርሌቨርኩዘን ይጫወታሉ፡፡

በማግስቱ ማክሰኞ ደግሞ የዩክሬኑ ሻክታር ዶኔስክ ከስዊዘርላንዱ ባዜል እንዲሁም ወልቭስ ከስፔኑ ሲቪያ ይገናኛሉ፡፡

የመልስ ጨዋታዎቹ ከአምስት ቀናት በኋላ ሲካሄዱ በደርሶ መልስ አሸናፊ የሚሆኑት በግማሽ ፍጻሜ እርስ በርስ ተጫውተው አሸናፊዎቹ ለፍጻሜ ያልፋሉ፡፡

ጨዋታዎቹ በጀርመን ኮሎኝ የሚደረጉ ይሆናል፡፡