የሀገር ውስጥ ዜና

የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ በክልሉ ባጋጠመው ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ግምገማ እያካሄደ ነው

By Tibebu Kebede

August 08, 2020

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 2 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ በክልሉ ባጋጠመው ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ግምገማ እያካሄደ ነው፡፡

ግምገማው በክልሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ እየተካሄደ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

በግምገማው ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እንዲሁም ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡