የሀገር ውስጥ ዜና

የዋና ከተማ የድንገተኛ አደጋና ጽኑ ህክምና ማሻሻያ መርሃ ግበር ተጀመረ

By Tibebu Kebede

August 08, 2020

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዋና ከተማ የድንገተኛ አደጋ እና ጽኑ ህክምና ማሻሻያ መርሃ ግብር በዛሬው እለት መጀመሩን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

የድንገተኛ አደጋ እና ጽኑ ህክምና ማሻሻያ መርሃ ግብሩ ከከተማ አስተዳደሮች፣ የዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሎችና ከክልል ጤና ቢሮዎች ጋር በመተባበር በ5 ዋና ከተሞች ላይ ዛሬ መጀመሩንም ዶክተር ሊያ በፌስቡክ ገፃቸው ባወጡት መረጃ ያመስታወቁት።

የፕሮግራሙ ዓላማ ጥራቱን የጠበቀ ድንገተኛ ህክምናን በዘላቂ ሁኔታ ለመስጠት የሚያስችል ሥርዓት መገንባት መሆኑንም ገልፀዋል።

ይህም በከተማ አቀፍ ቅንጅት፣ በቅድመ ሆስፒታል አገልግሎቶች እና በሪፈራል ስርዓቶች ላይ ያተኩራል ብለዋል የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ።

የዋና ከተማ የድንገተኛ አደጋ እና ጽኑ ህክምና ማሻሻያ መርሃ ግብሩ ስኬታማነቱ ሲረጋገጥም ወደ ሌሎች ከተሞች የሚስፋፋ ይሆናል ብለዋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።