የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ በ24 ሰዓታት 801 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የ10 ሰዎች ሕይወት አልፏል

By Tibebu Kebede

August 08, 2020

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 10 ሺህ 919 የላብራቶሪ ምርመራ 801 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 22 ሺህ 253 መድረሱንም የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ባወጡት መረጃ አመላክተዋል።