የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ መልካም ሥራዎች እና ተነሳሽነቶችን ማስፋፋትና ማጠናከር እንደሚገባ ገለፁ

By Feven Bishaw

August 09, 2020

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ መልካም ሥራዎች እና ተነሳሽነቶችን ማስፋፋትና ማጠናከር እንደሚገባ ገለፁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ የቆሻሻ መጣያ ስፍራዎችን በፈቃደኝነት ወደተስማሚ መስክ መለወጥ ለእይታ ብቻ ሳይሆን ለከተማ እርሻ ተግባራዊነት ማሻሻል የሚያስመሰግን ነው ብለዋል፡፡

እንደዚህ ያሉ መልካም ሥራዎች እና ተነሳሽነቶችንም ማስፋፋትና ማጠናከር አለብን ሲሉም አሳስበዋል፡፡

https://www.facebook.com/PMAbiyAhmedAli/videos/866862640509314/?epa=SEARCH_BOX