ኮቪድ 19 ለመመርመር የሚውሉ 100 ሺህ ኪቶች በድጋፍ ተገኙ
አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 3 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ኮቪድ 19 ለመመርመር የሚውሉ 100 ሺህ ኪቶች በድጋፍ መገኘታቸውን አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ ÷ዛሬ በልገሳ የቀረቡ 100 ሺህ መመርመሪያ ኪቶችን ተረክበናል ብለዋል።
አያይዘውም የኮቪድ 19 ምርመራን በስፋት በምናካሂድበት በዚህ ወቅት፣ የአጋሮቻችን ድጋፍ ስላልተለየን እናመሰግናቸዋለንም ነው ያሉት ።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።