ዓለምአቀፋዊ ዜና

ቻይና ከፍተኛ ባለስልጣናትን ጨምሮ በ11 አሜሪካውያን ላይ ማዕቀብ ልትጥል ነው

By Meseret Awoke

August 10, 2020

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 4፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ከፍተኛ ባለስልጣናትን ጨምሮ በ11 አሜሪካውያን ላይ ማዕቀብ እንደምትጥል አስታወቀች::

የሃገሪቱ መንግስት አሜሪካ ቤጂንግ በሆንግ ኮንግ ጉዳይ እየፈጸመችው ነው ላለችው የህግ ጥሰት በቻይናውያን ላይ ለጣለችው ማዕቀብ የተሰጠ አፀፋዊ ምላሽ ነው ብሏል፡፡

ከዚህ ቀደም አሜሪካ ቻይና በሆንግ ኮንግ የፖለቲካ ነጻነትን ገድባለች በሚል በ11 የቻይና ባለሥልጣናት እና አጋሮቻቸው ላይ ማዕቀብ መጣሏ ይታወሳል፡፡

የሪፐብሊካኑ ቴድ ክሩዝ እና ማርኮ ሩቢዮ እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ድርጅት ከፍተኛ ሃላፊዎች የማዕቀቡ ሰለባ ናቸው ተብሏል፡፡

ማዕቀቡ የትራምፕ አስተዳደር ባለስልጣናት ላይ ትኩረት አላደረገም ነው የተባለው ፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ