የሀገር ውስጥ ዜና

የሶማሌ ክልል በጎርፍ አደጋ ለተጎዳው የአፋር ክልል እርዳታ ሰጠ

By Feven Bishaw

August 10, 2020

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 4 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሶማሌ ክልል መንግስት በተፈጥሮ የጎርፍ አደጋ ለተጎዳው የአፋር ክልል እርዳታ ሰጠ።

ክልሉ 300 ካርቶን የምግብ ዘይት፣ 350 ኩንታል ዱቄት፣ 566 ኩንታል ሩዝ፣ 620 ብርድ ልብሶች፣ 520 የዝናብ መከላከያ ሸራዎች እንዲሁም የጤና ባለሞያዎችን ጭምር መላኩን ከክልሉ የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።